ልጆች እየተዝናኑ ማንበብ እንዲማሩ የሚረዳ መማሪያ ጌም
ሞንስተራችሁን አብሉት/Feed The Monster መሰረታዊ የማንበብ ክህሎትን የሚያስተምር ነው:: በዚህ ጌም፣ ልጆች የዳይኖሰሩን እንቁላሎች እየሰበሰቡ ፊደልና ቃላትን ይመግቧቸዋል በሂደትም እንቁላሉ ይፈለፈልና አዲስ ጓደኛቸው ይሆናል::
ልጆች የፊደላትን ሥርዐተ-ሆሄ እንዲያውቁ እና ቃላትን እንዲያነቡ ይማራሉ:: ይሄን ጌም በመጫወታቸውም ልጆች በትምህርታቸው ይጎብዛሉ እንዲሁም ቀላል ፅሁፎችን ለማንበብ ዝግጁ ይሆናሉ:: የኛም ፍላጎት ልጆችዎን እንዲማሩና ስኬታማ እንዲሆኑ ማዘጋጀት ነው::
ሞንስተራችሁን አብሉት 100% ነፃ ነው:: አንዴ ከተጫነ በኋላ ምንም አይነት የኢንተርኔት ዳታ ኮኔክሽን አያስፈልገውም! ለማስተማሪያነት የተሰራውም ለትርፍ ባልተቋሙት ሲኢቲ፣ አፕ ፋክቶሪ፣ እና ኪውሪየስ ለርኒንግ አማካኝነት ነው::