We use cookies and other technologies on this website to enhance your user experience.
By clicking any link on this page you are giving your consent to our Privacy Policy and Cookies Policy.

Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ Скриншоты

Oписание Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ

Первая полная эфиопская православная библия на геэзском, амхарском и английском языках.

በይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ ጠብቆ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብሉይና መጻሕፍት መጻሕፍት ብላ በ 1962 г. ዓ.ም ያሳተመችውን መጽሐፍ ቃል በቃል ለቅሞ መዝግቧል።

መጽሐፉ ለሃይማኖት አባቶች ለሰባክያነ ወንጌልና ለመምህራን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በሚሰማሩበት መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው መያዝ ሳይኖርባቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ጉልህ ይኖረዋል :: ምዕመናንም የግዕዙንና የአማርኛውን ትርጉም ምሥጢሩ ሳይዛባ እንዲጠቀሙ ይረዳል ::

የመጽሐፉ ልዩ ባሕርያት

• ሰማንያ አንድ (81) መጻሕፍትን ያካተተ ነው።

• ሙሉ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግዕዝ ፣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ነው።

• የአማርኛው ትርጉም በጥንታዊው የአባቶቻችን አጻጻፍና አገላለጽ ሃይማኖታዊ ለዛውን ሳይለቅ የተጻፈ ነው።

• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸውን የብሉይና የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍትን ያካተተ ነው።

• ፊደሉና አጻጻፉ በግእዝና በአማርኛ መዛግብተ ቃላት መሠረት ታርሞ የተዘጋጀ ነው።

• የፊደሎችን መጠን በቀላሉ ማስተካከያ መንገድ አለው።

• በቀንና በጨልማ ለማንበብ የራሱ ማስተካከያ ተካቶበታል።

• ማስታወሻ መያዣ ፣ ማቅለሚያ ፣ ዕልባት ማድረጊያ ተካቶበታል።

• ማጣቀሻዎች በየቁጥሩ የተካተቱ ሲሆን በቀላሉ አንድ ጊዜ ብቻ ጠቅ በማድረግ ገጹን ሳይለቁ ማንበብ ያስችላል።

• በጣም ፈጣንና የፍለጋ ውጤቶችን በማቅለምና በቁጥር የሚያሳይ መፈለጊያ ተካቶበታል።

• የአማርኛ ፣ የግእዝና የእንግሊዝኛ ዕትሞችን ጎን ለጎን ፣ መስመር በመስመር ፣ ከላይና ከታች አድርገን ለማንበብ ያስችላል።

• የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በአኅጽሮት ወይም በሙሉ ስም ለመዘርዘር ማስተካከያ ተደርጎበታል።

• የፊደል መጠኑን በቀላሉ ማሳነስና ማሳደግ የሚያስችል ማስተካከያ ተካቶበታል።

• የመጽሐፍ ቅዱስ መስመሮችን እንድፍላጎትዎ ማስተካከል ይችላሉ።

• ከዚህ በፊት ያነበቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከዚህ በፊት የተነበቡ በሚለው ስር ያገኟቸዋል።

• የተለያዩ ቋንቋዎችን በመጠቀም የመጽሐፉን ይዘት መተርጎም ይችላሉ።

ከ 66 ቱ መጻሕፍት በተጨማሪ 19 የብሉይ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት እና 8 የአዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍትን በግእዝና በአማርኛ አሟልቶ ተዘጋጅቷል።

የብሉይ ኪዳን ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት

1. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል

2. መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ

3. መጽሐፈ ጦቢት

4. መጽሐፈ ዮዲት

5. መጽሐፈ አስቴር

6. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ፣ ካልእና ሣልስ

9. መጽሐፈ ሲራክ

10. ጸሎተ ምናሴ

11. ተረፈ ኤርሚያስ

12. ሶስና

13. መጽሐፈ ባሮክ

14. መጽሐፈ ጥበብ

15. መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ

16. ተረፈ ዳንኤል

17. መጽሐፈ ኩፋሌ

18. መጽሐፈ ሔኖክ

19. መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን

የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት

⒈ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ

⒉ መጽሐፈ አብጥሊስ

⒊ ግጽው ዘሲኖዶስ

⒋ ሥርዓተ ጽዮን

⒌ መጽሐፈ ዲድስቅልያ

⒍ መጽሐፈ ትእዛዝ

⒎ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ እና ካልእ

ያውርዱና ብዙ የተደከመበትን መጽሐፍ ቅዱስ በእጅዎ ያስገቡ።

Что нового в последней версии 6.1.1

Last updated on 28/04/2021

በዚህ ዕትም ከዚህ በፊት ያልተጠናቀቁ መጻሕፍት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ተካተዋል። እነዚህም
⒈ መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን
⒉ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
⒊ መጽሐፈ አብጥሊስ
⒋ ግጽው ዘሲኖዶስ
⒌ ሥርዓተ ጽዮን
⒍ መጽሐፈ ዲድስቅልያ
⒎ መጽሐፈ ትእዛዝ
⒏ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ
⒐ መጽሐፈ ኪዳን ካልእ

Загрузка перевода...

Дополнительная информация о Приложения

Последняя версия

Запросить Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ обновление 6.1.1

Загрузил

Ahmed Elraman

Требуемая версия Android

Android 4.1+

Ещё
Язык
Подпишитесь на APKPure
Будьте первым, кто получит доступ к раннему выпуску, новостям и руководствам лучших игр и приложений для Android.
Нет, спасибо
Подписаться
Подписка оформлена!
Теперь вы подписаны на APKPure.
Подпишитесь на APKPure
Будьте первым, кто получит доступ к раннему выпуску, новостям и руководствам лучших игр и приложений для Android.
Нет, спасибо
Подписаться
Подписаны!
Теперь вы подписаны на нашу рассылку.