We use cookies and other technologies on this website to enhance your user experience.
By clicking any link on this page you are giving your consent to our Privacy Policy and Cookies Policy.

Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ Screenshots

Over Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ

De eerste complete Ethiopische Othodox Bijbel in Geez, Amhaars en Engels.

በይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ደንብ ጠብቆ የተዘጋጀ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዲሁም የቀኖና መጻሕፍት ብላ በ 1962 ዓ.ም ያሳተመችውን መጽሐፍ ቃል በቃል ለቅሞ መዝግቧል።

መጽሐፉ ለሃይማኖት አባቶች ለሰባክያነ ወንጌልና ለመምህራን ለመንፈሳዊ ተልዕኮ በሚሰማሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው መያዝ ሳይኖርባቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል :: ምዕመናንም የግዕዙንና የአማርኛውን ትርጉም ምሥጢሩ ሳይዛባ በስልካቸው እንዲጠቀሙ ይረዳል ::

የመጽሐፉ ልዩ ባሕርያት

• ሰማንያ አንድ (81) መጻሕፍትን ያካተተ ነው።

• ሙሉ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በግዕዝ ፣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ነው።

• የአማርኛው ትርጉም በጥንታዊው የአባቶቻችን አጻጻፍና አገላለጽ ሃይማኖታዊ ለዛውን ሳይለቅ የተጻፈ ነው።

• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸውን የብሉይና የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍትን ያካተተ ነው።

• ፊደሉና አጻጻፉ በግእዝና በአማርኛ መዛግብተ ቃላት መሠረት ታርሞ የተዘጋጀ ነው።

• የፊደሎችን መጠን በቀላሉ ማስተካከያ መንገድ አለው።

• በቀንና በጨልማ ለማንበብ የራሱ ማስተካከያ ተካቶበታል።

• ማስታወሻ መያዣ ፣ ማቅለሚያ ፣ ዕልባት ማድረጊያ ተካቶበታል።

• ማጣቀሻዎች በየቁጥሩ የተካተቱ ሲሆን በቀላሉ አንድ ጊዜ ብቻ ጠቅ በማድረግ ገጹን ሳይለቁ ማንበብ ያስችላል።

• በጣም ፈጣንና የፍለጋ ውጤቶችን በማቅለምና በቁጥር የሚያሳይ መፈለጊያ ተካቶበታል።

• የአማርኛ ፣ የግእዝና የእንግሊዝኛ ዕትሞችን ጎን ለጎን ፣ መስመር በመስመር ፣ ከላይና ከታች አድርገን ለማንበብ ያስችላል።

• የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በአኅጽሮት ወይም በሙሉ ስም ለመዘርዘር ማስተካከያ ተደርጎበታል።

• የፊደል መጠኑን በቀላሉ ማሳነስና ማሳደግ የሚያስችል ማስተካከያ ተካቶበታል።

• የመጽሐፍ ቅዱስ መስመሮችን እንድፍላጎትዎ ማስተካከል ይችላሉ።

• ከዚህ በፊት ያነበቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከዚህ በፊት የተነበቡ በሚለው ስር ያገኟቸዋል።

• የተለያዩ ቋንቋዎችን በመጠቀም የመጽሐፉን ይዘት መተርጎም ይችላሉ።

ከ 66 ቱ መጻሕፍት በተጨማሪ 19 የብሉይ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት እና 8 የአዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍትን በግእዝና በአማርኛ አሟልቶ ተዘጋጅቷል።

የብሉይ ኪዳን ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት

1. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል

2. መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ

3. መጽሐፈ ጦቢት

4. መጽሐፈ ዮዲት

5. መጽሐፈ አስቴር

6. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ፣ ካልእና ሣልስ

9. መጽሐፈ ሲራክ

10. ጸሎተ ምናሴ

11. ተረፈ ኤርሚያስ

12. ሶስና

13. መጽሐፈ ባሮክ

14. መጽሐፈ ጥበብ

15. መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ

16. ተረፈ ዳንኤል

17. መጽሐፈ ኩፋሌ

18. መጽሐፈ ሔኖክ

19. መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን

የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት

⒈ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ

⒉ መጽሐፈ አብጥሊስ

⒊ ግጽው ዘሲኖዶስ

⒋ ሥርዓተ ጽዮን

⒌ መጽሐፈ ዲድስቅልያ

⒍ መጽሐፈ ትእዛዝ

⒎ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ እና ካልእ

ያውርዱና ብዙ የተደከመበትን መጽሐፍ ቅዱስ በእጅዎ ያስገቡ።

Wat is er nieuw in de nieuwste versie 6.1.1

Last updated on Apr 28, 2021

በዚህ ዕትም ከዚህ በፊት ያልተጠናቀቁ መጻሕፍት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ተካተዋል። እነዚህም
⒈ መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን
⒉ መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
⒊ መጽሐፈ አብጥሊስ
⒋ ግጽው ዘሲኖዶስ
⒌ ሥርዓተ ጽዮን
⒍ መጽሐፈ ዲድስቅልያ
⒎ መጽሐፈ ትእዛዝ
⒏ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ
⒐ መጽሐፈ ኪዳን ካልእ

Vertaling Laden...

Aanvullende APP -informatie

Laatste Versie

Verzoek update van Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ 6.1.1

Geüpload door

Ahmed Elraman

Android vereist

Android 4.1+

Meer Info
Talen
Abonneer u op APKPure
Wees de eerste die toegang krijgt tot de vroege release, nieuws en gidsen van de beste Android -games en apps.
Nee bedankt
Aanmelden
Succesvol ingeschreven!
Je bent nu geabonneerd op APKPure.
Abonneer u op APKPure
Wees de eerste die toegang krijgt tot de vroege release, nieuws en gidsen van de beste Android -games en apps.
Nee bedankt
Aanmelden
Succes!
Je bent nu geabonneerd op onze nieuwsbrief.