Usar la aplicación APKPure
Obtener Metsihafe Sinksar መጽሐፈ ስንክሳር versión histórica en Android
የቅዱሳንን ተጋድሎ ፣ ክርስቲያናዊ ፅናትና ግብር በአጠቃላይ ገቢረ ገድላቸወንና ትሩፋታቸውን የሚዘክር መጽሐፍ ነው ፡፡
መጽሐፈ ስንክሳር አስተጋብአ (ሰበሰበ) ከለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን አስተጉቡእ (ስብስብ) ማለት ነው ፡፡ ጥርቅምቅም ውጥንቅጥ የተቀያየጠ መድበል የተደባበለ ነገር ማለት ነው።
የሥላሴን አንድነትና ሦሥትነት ÷ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቅድመ ዓለም ያለእናት ከበሕርይ አባቱ ከአብ ÷ ድኅረ ዓለም ያለአባት ከእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወሐዱን ÷ የመላእክትን ማዕርግና ሹመት የሚያስረዳ የነቢያትንና የሐዋሪያትን የጻድቃንንና የሰማዕታትን የደናግልንና የመነኮሳትን ምግባር መከራና እረፍት ከዕለት እስከ ዓመት የሚነገር መጽሐፍ ነውየቤተ ክሲያንን ታሪክ ÷ የመቤታችንን ዜና የልጇንም በጎ ሥራ ኹሉ በሰፊው ይናገራል። ትርጓሜውም በጽርእ የተሰብሰበ ስብስብ ማለት ነው። የቅዱሳን ነቢያትንና ሐዋርያትን ÷ የቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታትን ÷ ሀይማኖታዊ ተጋድሎ ÷ ክርስቲያናዊ ፅናትና ግብር በአጠቃላይ ገቢረ ተአምራታቸውን ÷ ገድላቸወንና ትሩፋታቸውን የሚዘክር ዕለተ መታሰቢየቸውንም የሚጽሐፍ መጽሐፍ ነው ፡፡ ጠቅለል ባለ ቋንቋ መጽሐፈ ስንክሳር ዝክረ ቅዱሳን መጽሐፍ ነው ፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ከመጻሕፍተ ብሉያትና ሐዲሳት ÷ ከገድላትና ድርሳናት የተቀዳ በቤተ ክርስቲያን በየቀኑ የሚነበብ ዜና ቅዱሳን ነዉ ፡፡
የመጽሐፉ ስም ከዓመት እስከ ዓመት የሚነበብ የቅዱሳን ዜና ከየገድላቸው ባጭር ባጭር ቃል የተሰበሰበ እሉድ ምእላድ እስትጉቡእ ማለት ነው ፡፡
እስከ ዓመት በአሉት ዕለታት የሞቱ የነቢያትን የሐዋርያትን የሰማዕታትን የጻድቃንን የመነኮሳት የደናግል በእግዚአብሔር ስም ለዐረፉ ታሪካቸውና ገድላቸው የተጻፈበት ወይም የሞቱበትንም ቀን የሚዐሳስብቀ መጽሐፈ ስንክሳር መድበል።
Last updated on 22/08/2024
Minor bug fixes and improvements. Install or update to the newest version to check it out!
Requisitos
5.0
Categoría
Reportar
Metsihafe Sinksar መጽሐፈ ስንክሳር
4.0.2 by Goranda Apps
22/08/2024
$4.99