Use APKPure App
Get Gibre Himamat ግብረ ሕማማት old version APK for Android
መጽሐፈ ግብረ ሕማማት ምስለ ጾመ ድጓ
جيبري همامات هو كتاب إثيوبي أرثوذكسي توهيدو يُقرأ في الأسبوع المقدس ، الأسبوع الأخير من زمن الصوم الكبير. يحتوي الكتاب على قراءات النخيل الأحد ، الاثنين المقدس ، الثلاثاء المقدس ، الأربعاء المقدس (الجاسوس الأربعاء) ، خميس العهد (الخميس المقدس) ، الجمعة العظيمة (الجمعة المقدسة) ، السبت المقدس وعيد الفصح. يحتوي الكتاب على قراءات من الكتاب المقدس ، والكتب الكنسية الأرثوذكسية ، والكنائس ، ومعجزات يسوع المسيح ، ومعجزات القديسة مريم ، والنبوءات ، وكتب الصلاة ، و Haymanote Abew ، والصلاة من العهد ، Gedles والمزيد من كتب الكنيسة الإثيوبية الأرثوذكسية Tewahedo.
الغرض السري من هذا الكتاب هو تذكيرنا بأن الرب قد ألحق بنا الألم والموت والحرية الأبدية والمجد في قيامته ، وأنه إله الحياة بدون ألم وموت ، يقرأ ويتدرب كل يوم في هذا الأسبوع المقدس
وبناءً على ذلك ، فإن النمط العام للصلاة وخدمة جبري همامات وارد في هذا الكتاب ، ويحدونا أمل صادق في أن يتمكن الكهنة والأبرشيات من الإمساك بالكتاب ومتابعته.
መጽሐፈ ግብረ ሕማማት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታችንነ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀል የሚዘከርበትና በሰሙነ ሕማማት የሚነበብ ታላቅ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ፣ ከሥርዓት መጻሕፍት ፣ ከትንቢት ፣ ከድርሳናት ፣ ከተአምራት ፣ ፣ ከሃይማኖተ አበው ፣ ከኪዳን ከኪዳን ፣ መጻሕፍት መጻሕፍት የተውጣጡ ትምህርቶችንና የጸሎት ክፍሎችን ከሆሣዕና ዋዜማ እስከ ትንሣኤ ባሉት ስምንት ቀናንት በሰዓታት ተከፋፍሎ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።
የመሠረቱና ታሪካዊ አመጣጡም ከአባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ተያይዞ የመጣ ነው። ይኸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለሐዋርያት እየተገለጸ እስከ አርባ ቀን ድረስ መጽሐፈ ኪዳንንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምራቸው ቈይቶ። በአርባ ቀኑም ሐዋርያትን በአንብሮተ እድ ሹሟቸውና ባርኳቸው አርጓል። (ማር ፲፮ ፲ህ። ሉቃ ፳፬ ፤ ፶፩። የሐዋ ሥራ ፩-፱)
ከዚህም በኋላ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ካሉ ምዕመናን ጋር ጾም መጾምንና ትንሣኤውን ማክበር ጀመሩ። በዚህ ጊዜ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው በደነገጉት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፥ ስለ ሰሙነ ሕማማት «ወአንትሙሰ ተዐቅቡ ወግበሩ ተዝካረ ሕማማቲሁእናንተ ግን ጠብቃችሁ የመከራ መስቀሉ መታሰቢያ የሆነውን ሕማማቱን አድርጉ አክብሩ» ሲሉ አዝዘዋል። (ትእዛዝ ፴፩)
ሆኖም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ይፋጠኑ ነበረና እንደ ዛሬው ሁሉ ጊዜውን አልወሰኑትም ነበር። ከሐዋርያት ቀጥለው የተነሱ ሊቃውንትም ቢሆኑ እንደዚሁ በዐተ ጾምን ከጥር ፲፩ ቀን እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ከጾመ። በኋላ ሰሙነ ሕማማትን ደግሞ ከዐቢይ ጾም ለይተው ከመጋቢት ፳፪ እስከ መጋቢት ፳፰ ቀን በመጾም መጋቢት ፳፱ ቀን ትንሣኤውን ያከብሩ ነበር። ይህ ሥርዓት ሲያያዝ እስከ ድሜጥሮስ ዘመን ደረሰ።
ከ፩፻፹፰ እስከ ፪፻፴ ዓ.ም የነበረው ሊቀ ጳጳስ ድሜጥሮስ በአዘጋጀው የጊዜ መቁጠሪያ (ባሕረ ሐሣብ) ሰሙነ ሕማማት ከዐቢይ ጾም ቀጥታ እንዲሆን ተወስኖአል። ቤተ ክርስቲያንም በቀመረ ድሜጥሮስ ዓመታትን በንዑስ ፤ በማዕከላዊና በዐቢይ ቀመር እየቀመረች አጽዋማት የሚገቡበትንና በዓላት የሚውሉበትን ጊዜ ለምዕመናን ታሳውቃለች።
ስለሆነም የሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎትና አገልግሎት ሁኔታ ከቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮት ጋር የተያያዘ ቢሆንም የያዘ ሕማማት ሕማማት ፤ ፤ መጽሐፍ ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ የዋለው ከጌታ ልደት በኋላ በ፲፬ኛው ምዕት ዓመት ነው።
ከ፩ሺ፫፻፵ እስከ ፩ሺ፫፻፹ ዓ.ም የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ብርሃነ ዐዜብ ከዐረብኛ ወደ ግእዝ እንደተረጎሙት ቀደም ሲል በግእዝ ብቻ ታትሞ በነበረው የግብረ ሕማማት መጽሐፍ ውስጥ ተገልጦአል።
የመጽሐፉ ስያሜም ከጥንተ ስሙ ጀምሮ ግብረ ሕማማት እንደሚባል በመጽሓፉ ውስጥ በብዙ ክፍል ተጠቅሶ ይገኛል። ለዚሁም በቂ የሆነ ምሥጢራዊ ምክንያት እንዳለው ይታመናል።
ምሥጢራዊ ዓላማውም ጌታ በሕማሙ ሕማማችንን ፤ በሞቱ ሞታችንን ፤ በትንሣኤው ዘለዓማዊ ነፃነትንና ክብርን ያጐናጸፈን መሆኑን ከማስገንዘቡም ሞት የሌለበት የሌለበት ባሕርይ አምላክ መሆኑ በሰሙነ ሕማማት በየአንዳንዱ ቀን ይነበባል ይተረካልም።
በዚህ መሠረት የሰሙነ ሕማማት ጸሎትና አገልግሎት ጠቅላላ ሥርዓት በዚህ መጽሓፈ ግብረ ሕማማት በየክፍሉ ተጽፎ ስለሚገኝ ካህናትም ምዕመናንም መጽሐፉን በመያዝ ሥርዓቱን ለመከታተል ያመቻል የሚል ጽኑእ ተስፋ አለን።
Last updated on 22/08/2024
Minor bug fixes and improvements. Install or update to the newest version to check it out!
Android متطلبات النظام
5.0
الفئة
الإبلاغ
Gibre Himamat ግብረ ሕማማት
5.2.1 by Goranda Apps
22/08/2024
$4.99